፠ ለኦርቶዶክስ ጋብቻ መመሪያ ፠
በታሪክ ውስጥ ስንመለከት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስቀድመው በአንድ ቦታ ከነበሩ ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓቶች ጋር ጥንቃቄ የተሞላበት ግንኙነት መሥርታ፤ በዚህም ውስጥ ኦርቶዶክሳዊነት ቀድመው ከነበሩት ሥርዓቶች ጋር ሲነጻጸር ያለውን ሁለንተናዊ ብልጫ እና በአዳዲስ አማኞችም ዘንድ እውነተኛውን የክርስትና መልእክት በተገቢው መንገድ ለማስረጽ ባለመ ሁኔታ ውስጥ ወንጌልን ለማሰራጨት ብዙ ሠርታለች፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች እንዲያውም፤ የአካባቢው ቀደምት አካሄድ የክርስትና መልእክትን የማይጋፋ ሆኖ ከተገኘ ወይንም ደግሞ ቤተክርስቲያኒቷ ለአዳዲስ አማኒያን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ላለመፍጠር ስትል ነባር ሥርዓቶችን አቅፎ የመጓዝ አካሄድን የተጠቀመችበት ሁኔታ አለ[1]፡፡ በዚህም ምክንያት አስቀድመው የነበሩ ማኅበረሰባዊ አወቃቀሮች በክርስትና ሳይዋጡ አብረው መጓዝ ችለዋል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች እና ማኅበረሰቦች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶች ነባር እሳቤዎቹን ይገነዘቧቸው የነበረ ሲሆን አላስፈላጊ የሆኑትንም በግልጽ ይኮንኑ ነበር፡፡ ለዚህም እንደ አብነት የሚጠቀሰው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባርነትን የኮነነበት መንገድ ነው[2]፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰቦች ውሰጥ ከዘመኑ ታሪክ ጋር ተያይዘው ያሉት ማኅበረሰባዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኩነቶች፤ በወቅቱ ነገረ-መለኮታዊ ትምህርቶች በካህናት እና አገልጋዮች የሚታዩበትን መንገድ እና በካህናቱ በኩል ለምዕመኑ የሚደርሱበት ዘዴ ላይ ተጽእኖን ማሳደራቸው አይቀርም[3]፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በገነነችባቸው አካባቢዎች ላይ የሚካሄዱ ውይይቶች እና ስብከቶች ከፖለቲካዊ፣ ማኅበረሰባዊ፣ ባህላዊ እና ሌሎችም የተለያዩ አቅጣጫዎች አንጻር እንዲቃኙ በመሆናቸው ለመበረዝ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች፤ የኦርቶዶክስ አባቶች ምንም እንኳ በተለያየ ዘመን ቢኖሩም፤ ያንጸባርቁት ከነበረው እና ታሪካዊ መሠረት ካለው ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ (ፍሮኒማ) ተለየቶ ሊታይ ይገባዋል፡፡
[1]
ይህ አካሄድ የሚታየው ቅዱስ ጳውሎስ ‹ለማይታወቅ
አምላክ› በሚል የተጻፈውን የግሪክ ጽሑፍ መሠረት አድርጎ አቴናውያንን ለክርስትና ሲያስተዋውቅ ነው፡፡(ሐዋ 17፡23)
[3]
ለአብነት ያህል፡-
ታሪካዊ የሩሲያ
ኦርቶዶክስ
ምዕመናንን
በተመለከተ
ኤልሳቤጥ
ጋዚን ስትጽፍ
እንዲህ
ትላለች - ‹‹እነዚህ
ማኅበረሰቦች
ኦርቶዶክስ
ይባሉ
እንጂ፣
የአካባቢው
ዘመናዊ
ታሪክ
ቃኝተን
ቤተክርስቲያን
ልጆቿን
በተገቢው መንገድ
እንድታስተምር
የማይፈቅዱ
ኢስላማዊ
እና
ኮሚኒስት ኃይሎች
እንደነበሩባት
ስንረዳ፤ ከዚህ
አንጻር
እውነተኛው
ኦርቶዶክሳዊ
ኤቶስ-ባሕርይ
ምን ያህል
በእነዚህ
ማኅበረሰቦች
ውስጥ
ሊገኝ
እንደሚችል
ጥያቄ
ማንሳታችን
አይቀርም፡፡››
የሚከተለውን
ምንጭ
ይመልከቱ፡- Elizabeth
Gassin, “Eastern
Orthodox
Christianity and
Men’s
Violence against
Women” in
Religion
and Men’s Violence against Women, A. Johnson,
ed. (Springer:
New York,
2015), 165.
|