ቅድስት
ማክሪና
በከፊል
ከሚከተለው
ድረገጽ
የተወሰደ፡
https://www.pemptousia.gr/2014/07/agia-makrina/ ‹‹ቅዱሳት
ሥዕላት›› - አፖስቶሊክዲያኮኒያ ኅትመት
|
በታሪክ መዛግብት ሆነ የቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ የታላላቅ ወንዶችን ብቻ ሳይሆን የታላላቅ ሴቶችንም ታሪክ መዝግቦ አቆይቶልናል፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ገላቲያ ምዕመናን የላከው መልእክት ውስጥ የሚገኘው ‹‹ወንድም ሴትም የለም…›› [ገላ 3፡28] የሚለውን ቃል በዚህ ቦታ መጥቀስ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በክርስቶስ ኅብረት ውስጥ ‹ወንድ› እና ‹ሴት› የሚል መለያ አለመኖሩን ነው፡፡ ሁለቱም ጾታዎች እኩል ዋጋ ያለቸው፣ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ እና የተከበሩም ናቸው፡፡ ገና በልጅነቷ ወላጅ አባቷ ለአንድ ጥሩ ወጣት ቢያጫትም፤ የትዳራቸው ቀን ሳይደርስ በፊት ወጣቱ በሞት ተለየ፡፡ ይህም ለማክሪና በቂ ነበር፡፡ ትዳሩ እንደተፈጸመ እና እንዳገባች ራሷን በመቁጠር፤ ለአባቷ ዐሳብ ታማኝ ሆና ቀጠለች፤ ወንድሞቿንም በማሳደግ ሒደት እናቷን በማገዝ ላይ አተኮረች፡፡ በቤት ውስጥም ወንድሞቿ እጅግ ያከብሯት እና እንደ ሁለተኛ እናት ያዩዋት ነበር፡፡ቅዱስ ባስልዮስ የነበረበትን የሕግ ሙያ በመተው ወደ ምንኩስና ሕይወት እንዲገባ ያሳመነችውም እርሷ ነበረች፡፡ አባቷ ከሞተ በኋላም ዘጠነኛ ወንድሟ የነበረውን ጴጥሮስን ማሳደግና በትምህርቱም መርዳት ጀመረች፤ ‹‹እጅግ ከፍተኛ ወደሆነ የእውቀት ደረጃ መራችው›› እንዲል፡፡ ይህ ወንድሟ በኋላ ላይ የሰቫስቲያ ሊቀ-ጳጳስ ሊሆን ችሏል፡፡ ሆኖም ግን ቅድስት ማክሪና ‹‹የሕይወት መምህር›› እና ‹‹ሁለተኛ እናት›› ብቻ አልነበረችም፤ ቅድስት የሆነች መነኩሴም ጭምር እንጂ፡፡ ሁሉም ወንድሞቿ ለአቅመ አዳም ደርሰው የራሳቸውን መንገድ ከያዙም በኋላ፤ በፖንተስ ከተማ ወደሚገኘው የቤተሰቦቿ ቤት በመሄድ ትልቅ የሴቶች ገዳምን መሠረተች፡፡ ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስም ‹የመልካም ምግባራት መማሪያ ቦታ› በማለት ስለሚጠራው ይህ ገዳም ሲናገር፡ ‹‹በመንፈሳዊ እናትነት የወለደቻቸው እና በትኩረትና ትጋትም ወደ ፍጹምነት ደረጃ ያደረሰቻቸው በዙሪያዋ የሚገኙት ደናግላን ብዙ ነበሩ፡፡ የመላእክትን ኑሮ በሰው ልጅ ሰውነት ኖራዋለች…›› እንዲል፡፡ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለማግኘት የራሳቸውን ሕይወት የተዉ ቅዱሳን ሴቶች…. ዝግጅት በ: ሮ. ኢ.፣ ፍ. አ. |